ቀን 6/8/2014 ዓ.ም

በቦሌ ክፍለ ከተማ ምስራቅ ድል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ኳስ ጨዋታ ተማሪዎችና የትምህርት ቤት ማህበረሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል ።

በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ፣የስፖርት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣  የትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሳምሶም መለሰ ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ፣  የትምህርት ቤቱ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም የሃገራችን ታዋቂ  ኮሚዲያኖች ተሳትፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶም መለሰ በትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና ተሳትፎዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁላችንም በጋራ የምንሰራው ቁልፍ ተግባራችን በመሆኑ አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ባደረጉት ንግግር  ስፖርታዊ እንቅስቃሴን  በየትምህርት ቤቶች የዘወትር ተግባር በማድረግ በተማሪዎች ላይ የዕርስ በርዕስ ግንኙነት እንዲጠናከር ከማድረግ ባሻገር  ተተኪ ስፖርተኞችን  እንደ ሃገር በመፍጠር በኩልም ትምህርት ቤቶች የማይተካ ሚና  ያላቸው በመሆኑ ቢሮው ዛሬም ለትምህርት ቤቶች ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ  በተጨማሪ በትምህርት ቤቱ  የእግር ኳስ ጨዋታ፣ እና ስፖርታዊ ትርዒቶች ተካሂዷል ።

የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አስረኛ ፕሮግራም ነገ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አሳይ  አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የስፖርት ቤተሰቦችና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል  ።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s