የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸምን ከቢሮ ስራተኞች ጋር ገምግመዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳስታወቁት የተከናወኑ ስራዎችን በየጊዜዉ እየገመገሙ መሄድ እና የነበሩ ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን መለየት በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ቁልፍ መሆናቸዉን በማንሳት ሁሉም ሰራተኛ ለተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎች ሚናዉ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ቢሮዉ ላከናውናቸዉ በእቅድ የያዛቸዉ የ2014 ዓ.ም ግቦች አፈጻጸም የዘጠኝ ወር ሪፖርት በቢሮዎ የእቅድ በጀት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌታሁን ለማ ቀርባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአዲሲ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቀጣይ ሶስት ወራት የአገልግሎት አስጣጥ እቅድ በቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ሲሳይ እንዳለ እንዲሁም የቢሮ ማህበራዊ ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት በአቶ መክብብ በለጠ አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ማተቃለያም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥታቸዉ ሊከናወኑ በሚገቡ ስራዎች ዙሪያም ከሰራተኛዉ ጋር ተደርሳል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
