የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ለአይሲቲ ባለሙያዎችና ተጠሪዎች ስልጠና በመስጠት ጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት በ2013 ዓ.ም አዳዲስና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ለተሰራላቸው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ለሚገኙ አይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት መስጠት ጀምራል፡፡
ስልጠናው አይሲቲ ባለሙያዎች መሰጠቱ የስኩልኔት ትግበራን እንዲሁም በትምህርት ቤቶች የተዘረጉ መሰረተ ልማቶችን አተገባበር በአግባቡ በመጠቀም የመማር ማስተማሩን ስራ የተሻለ ለማድረግ እንደሚያግዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ ገልጸዋል፡፡ አቶ በለጠ አክለውም ስልጠናው ትምህርት ቤቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት አሰራር ስርዓቶችን እንዲጠቀሙ ከማድረግም በተጨማሪ የፕላዝማ አጠቃቀምን በማዘመን የዋይፋይና ኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለተማሪዎች ለማድረስ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡
BESYS Trading & information system ተቋም የፕሮጀክት ጥገናና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ወንደሰን ሃይሌ በበኩላቸው ስልጠናውን ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር መስጠታቸው በባለሙያዎች ላይ የሚታዩ የእውቀት ክፍተቶችን ለመድፈንና ባለሙያዎች በሀላፊነት ስሜት ቀላል ጥገናዎችን በመስራት የትምህርት ስርዓቱ ሳይቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ብቁና እኩል ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው በሶስት ዙር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአይሲቲ ባለሙያዎችና የአይሲቲ ተጠሪዎች የሚሰጥ ሲሆን የአዲስ ከተማ ፣ ጉለሌና አራዳ ክፍለ ከተሞች በዚህ ዙር ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሆነ ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
