ቀን 3/8/2014 ዓ.ም

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና መልካም ስነ ምግባር የተላበሱ ዜጎችን ለመቅረጽ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አሳውቋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2014 ዓ/ም የ1ኛ መንፈቅ ዓመት የተማሪዎች ውጤት ትንተናን እንዲሁም በመንግሥትና በግል የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ባህሪ ላይ ያዘጋጀውን ጥናትና ምርምር በማቅረብ ውይይት አካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፤ በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና መምህራኖች ፣ የወላጅ ተማሪ መምህር ማህበር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በመማር ማስተማር ሂደት ተማሪዎች በተማሩት ትምህርት ምን ያክል በቅተዋል ወይም ወደ ሚቀጥለዉ ክፍል ለመሻገር ምን ያክል እዉቀትና ክህሎት ይዘዋል የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ የምንጠቀመዉ አንዱ መሳርያ ምዘና በመሆኑ የ2014 ዓ/ም የአንደኛ መንፈቅ አመት ምዘና  በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተከታታይ አጫጭር ምዘና እስከ የመንፈቅ አመቱ ማጠቃልያ ምዘና የተሰጠ መሆኑን እንዲሁም የተካሄደዉን የተማሪዎች ምዘና መሰረት በማድረግ  የተገኘው ዉጤት ተተንትኖ መቅረቡን የጽ/ቤቱ  ኃላፊ ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ  አስገንዝበዋል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና መልካም ስነ ምግባር የተላበሱ ዜጎችን ለመቅረጽ በስርዓተ ትምህርቱ ማዕቀፍ  በተቀመጠው መሰረት ብቁ ተማሪዎችን ለማፍራት፤ በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፓኬጅ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰፊ ስራዎች በመተግበር ላይ መሆናቸዉን ኃላፊዋ አክለው አሳውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s