የ2014 ዓ.ም የትምህርት መረጃን ወደ ዳታ ቤዝ ለማስገባት የሚያስችል የሶፍት ዌር ትውውቅ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አስተዳደርና መረጃ ስርዓት ዳይሬክቶሬት የ2014 ዓ.ም የትምህርት መረጃን ወደ ዳታ ቤዝ ለማስገባት የሚያስችል የሶፍት ዌር ትውውቅ ስልጠና መስጠቱን አሳታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አስተዳደርና መረጃ ስርዓት ደይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፋንታዬ እንደገለጹት የ2014 ዓ.ም የትምህርት ስታቲክስ መረጃን ወደ ደታቤዝ ለማስገባት የሚያስችል የሶፍተዌር ትውውቅ ስልጠና ለክፍለከተማ የመረጃ ቡድን መሪዎችና ባለሙዎች መሰጠቱን በመጥቀስ ሶፍትዌሩን በማስተዋወቅ ክፍለከተሞች የራሳቸውን ተቋም መረጃ እራሳቸዉ ወደ ዳታቤዝ እንዲያስገቡ እና በአግባቡ ማስቀመጥ እንዲችሉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ፍቃዱ አክለዉም ከስልጠናው በኋላ ባለሙያዎች ሶፍትዌሮችን በየኮምፒውተሮቻቸው ላይ በመጫን መረጃ የማስገባት ተግባራትን በማከናወን የመረጃ መዛባትን ለማስቀረት የሚስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ስልጠናዉ የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ የቢሮው ባለሙያዎች የተሰጠ መሆኑን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







