የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ለፍትሀዊነት(GEQIP -E) የስራ ክፍል ፕሮግራሙን ተግባራዊ ከሚያደርጉ የስራ ክፍል ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በፕሮግራሙ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ለፍትሀዊነት (GEQIP) ፕሮግራም ከአለም ባንክና ከሌሎች ለጋሽ ሀገራት በሚመደብ በጀት ከ2002ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 13 አመታት የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ በመተግበር ላይ የሚገኝ ፕሮግራም መሆኑን የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ለፍትሀዊነት ፕሮግራም አስተባባሪው አቶ አሸናፊ ከበደ አስታውቀዋል።
አስተባባሪው አክለውም ፕሮግራሙ ከ”ኦ” ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ባለው የትምህርት እርከን እንደሚተገበር ጠቁመው በዋናነትም ውስጣዊ የትምህርት ብቃትን ማሻሻል ፣ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ የድጋፍ መስጫ ማዕከላትን ማደራጀት፣ የመማሪያ መጽሀፍትን ጨምሮ የተለያዩ ቁስቁሶችን ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ የማድረግን ጨምሮ ለመምህራን ሙያዊ ብቃታቸውን የሚያሳድጉበትን ስልጠናዎች የመስጠት ስራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት ሶስተኛ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝና በጀቱም ውጤትን መሰረት አድርጎ የሚለቀቅ እንደመሆኑ ፕሮግራሙ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቶ አሸናፊ አሳስበዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




