በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ትምህር ጽ/ቤት ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል የሳይንስ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ዉድድር ተካሄደ፡፡
ውድድሩ በወረዳዉ ውስጥ በሚገኙ የግልና የመንግስት 16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ተካሄዳል፡፡
በዉድድሩ ላይ ተማሪዎች የሰዉን ልጅ የእለት ከእለት እንቅስቃሴን የሚያቀሉ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ኑሮ የሚያግዙ የፈጠራ ስራዎችን ይዘዉ ቀርበዋል፡፡
በተጨማሪም የስእልና የቅርሳቅርስ ዉጤቶች እና በርካታ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዉ በተማሪዎች ገለፃ ተደርጋል፡፡
በዉድድሩ ላይም ከ1 እስከ 3 ለወጡ ተማሪዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸዉ ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
በውድድሩ መጨረሻ ላይ የዋንጫ ሽልማት በሚያስገኘዉ በፊዚክስ፣ በኬምስትሪ እንዲሁም በባይሎጀ የትምህርት ዘርፎች በተደረገዉ ዉድድር መሰረትም ዳምቦስኮ ፣ ምህራፍ እንዲሁም ቆሬ ብርሀን ትምህርት ቤቶች በቅደም ተከተላቸው መሰረት ከ1ኛ እስከ 3 ኛ ደረጃ በመዉጣት የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን ችለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!











