የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ፎርም አሞላልና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንዳስታወቁት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተማሪዎች ቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወሰንበት የትምህርት እርከን መሆኑን ጠቁመው ትምህርት ቤቶች የተፈታኝ ተማሪዎቻቸውን አጠቃላይ መረጃ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በከፍተኛ ጥንቃቄ በመመዝገብ ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ2014 ዓ.ም የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ምዝገባ እና የምዝገባ ቅጽ አጠቃቆርን የተመለከተ መመሪያ ያቀረቡ ሲሆን በመመሪያውም የተማሪዎች መረጃ ፣ የትምህርት ቤቶችና የክፍለ ከተሞች ኮድ፤ የተመዝጋቢ ተማሪዎች መብትና ግዴታ የሚሉና ሌሎች መሰል ጉዳዮች መካተታቸውን አስታውቀዋል፡፡፡፡
በውይይቱ ከአዲስ ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ ፣ አራዳ ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌ እንዲሁም ቂርቆስ ክፍለከተሞች የሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና የክፍለከተሞቹ የሁለቱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ በነገው እለትም ከቀሪ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንደሚደረግ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
