የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ፤ በተፋጠነ የትምህርት ትብብር እና አጋርነት ስትራቴጂክ ማናል እና በሱፐርቪዥን አገልግሎት በተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ግምገማ አፈጻጸም ላይ እንዲሁም የቀጣይ ሶስት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ እንዲሁም በተፋጠነ የትምህርት ትብብር እና አጋርነት ስትራቴጂክ ማናል ላይ ገለጻ እና በሱፐርቪዥን አገልግሎት በተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክጽል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳስታወቁት የቀጣዩ ሶስት ዓመታት የትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል እቅድ ውጤታማ እንዲሆን ያለፈዉን የትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻል እቅድ አፈጻጸም በአግባቡ መገምገም ይገባል ብለዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም ስትራቴጂክ እቅዱ እና ግምገማዉ ተናባቢ ሊሆን እነደሚገባ አጽኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ከአዲስ ከተማ ፣ አቃቂ ቃሊቲ ፣ አራዳ ፣ ቦሌ ፣ ጉለሌ እንዲሁም ቂርቆስ ክፍለከተሞች የሚገኙ የመንግስትና የግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እና የክፍለከተሞቹ የሁለቱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ በነገው እለትም ከቀሪ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንደሚከናወን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




