በማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ምልከታ ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና የቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘዉ በማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት በመገኘት ምልከታ አካሂደዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘዉ ማሪፍ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር የሆኑት ሚስተር ኢሳ ሴቨር ትምህርት ቤቱ በቱርክ መንግስት በሚታገዘዉ ማሪፍ ፋውንዴሽን የሚተዳደር እንደሆነ በመግለጽ ፋውንዴሽኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 243 ትምህርት ቤቶችን እያስተዳደረ እንደሚገኝ አሳውቀዋል፡፡ ርዕሰ መምህሩ አክለዉም ትምህርት ቤቱ በትምህርት ዘርፍ ላይ የላቀ ድጋፍ ለመስጠት ከመንግስት ጎን ቆሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ አብይ ሀይሌ በበኩላቸዉ ማሪፍ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ከየካ ቅርንጫፍ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች በሲኤምሲ ፣ በአፍሪካ ህብረት ፣ በሳርቤት ፣ በሰበታ እና በሀረር እንዳሉት ገልፀዋል፡፡ አክለዉም ትምህርት ቤቱ በኢትዮጵያ እና በኢንተርናሽናል ሰርዓተ ትምህርት ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዉ በየካ በሚገኘዉ ትምህርት ቤት 231 ተማሪዎች ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ መሆናቸዉን አሳውቀዋል፡፡ አቶ አብይ አክለዉም ትምህርት ቤቱ ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከኬጂ እሰከ 12ኛ ክፍል ድረስ ማስተማር መጀመሩን በመግለጽ ተቋሙ ለተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ማዘጋጀቱን አሳውቀዋል፡፡
ነጻ ትምህርት እድሉ በሚቀጥለዉ ዓመት 5ኛ ፣ 9ኛ እና 11ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች በቀረዉ አጭር የመመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ኦላይን በመመዝገብ የተዘጋጀዉን ፈተና ተፈትነዉ የሚጠበቀዉን ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

