የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት በስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ላይ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡
በውጤት አምጪ የስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ያስቻል ስልጠና ከትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ 165 የቡድን መሪዎች ፣ ባለሙያዎች ፣ሱፐርቫይዘሮች ፣ ርዕሳነ መምህራን እና መምህራን መስጠቱን የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡
በውጤት አምጪ የስራ አሰራር ስርዓት እና በአመለካከት ለውጥ ዙሪያ ስልጠናው ያተኮረ እንደሆነ የጠቆሙት ሀላፊዋ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የተሻለ የስራ አሰራር ስርዓት ዘርግቶ ውጤታማ ከመሆን እና የተማሪዎቻችንን ውጤትና ስነ-ምግባር ከማሻሻል አኳያ ውስንነቶች በመታየታቸው ያንን ለመቅረፍም የተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
ከአነዚህ ችግሮች በመውጣት አመለካከትን በማዘመን እና በውጤት አምጪ አሰራሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የትምህርት ስርዓቱ የሚፈልገውን ብቁ ዜጋ ማፍራት እና ለሀገር ልማት እድገት ሚናውን የሚወጣ ትውልድ ለመቅረፅ የሚደረገውን ጥረትንም ስልጠናዉ ይደግፋል ተብሏል፡፡
የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላትን የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ያሉት ሀላፊዋ በዘርፉ ላይ የሚሰሩና በባለ ድርሻነት እየተሳተፉ ያሉ አካላት ጭምር በጋራ መስራት ወሳኝነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

