ቀን 1/7/2014 ዓ.ም

የትምህርት ቤት ምገባን ለማገዝ ከአንድ ማዕከል ግብዓቶችን ለማቅረብ እንዲቻል ስራ እየሰራ መሆኑን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አሳወቀ፡፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ለትምህርት ቤት መጋቢ እናቶች እፎይታን ለመፍጠር እንዲያግዝ እና ለሁሉም ት/ቤቶች ከአንድ ማእከል የእንጀራና የዳቦ አቅርቦት እንዲያገኙ የገበያ ትስስር እዲፈጠር ለማድረግ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በመሄድ የመስክ ምልከታ አድርጋል።

በመስክ ምልከታውም ላይ የክ/ከተማው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ እና በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተሳተፊ ሆነዋል።

የመስክ ምልከታ የተደረገበት ማን እንደእናት የእንጀራና የዳቦ መጋገሪያ ድርጅት ባለቤት የሆኑት አቶ አልዓዛር አሰፋ ልዑኩን ባስጎበኙበት ወቅት የድርጅታቸዉን ዋና አላማ ሲገልጹ እንደ ዜጋ ለተማሪዎች  ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ  ዋጋ በሰዓቱ  ማቅረብ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ የድርጅቱ ባለቤት አክለዉም አንድ እንጀራ በ7ብር እና አንድ ዳቦ ተገቢውን ግራም የጠበቀ በ3 ብር የሚያስረክቡ መሆኑን ይህም ዋጋ ካለው ወቅታዊ  የገበያ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር  የተሻለ እንደሆነ ለሙከራም ወረዳ 4 ለሚገኘዉ  አራብሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በማቅረብ ውጤታማ በመሆናችን አሁን ላይ አቅርቦታችንን ለሁሉም ት/ቤቶች ለማስፋት አሰፈላጊውን ግብዓት ሟማላታቸዉን  ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዋንኛነት የኃይል መቆራረጥ እንዳይገጥማቸዉ የራሳችን ትራንስፎርመር እና ጄኔሬተር ያስገጠሙ መሆናቸዉን ፣ በቂ የዳቦ ማሽኖችና የእንጀራ መጋገሪያ የኤሌክትሪክ  ምጣዶች ከበቂ የሰው ኃይል ጋር በማዘጋጀት በቀን 20ሺ እንጀራ እና 45ሺ ዳቦ በማምረት በራሳቸዉ ትራንስፖርት  በየት/ቤቶች እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት  ኃላፊ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የመጋቢ እናቶችን ድካም መቀነስ ሲሆን ሌላው ዘይትና ስኳር እንደዚሁ ከአንድ ማእከል እዲያገኙ ከሸማች ህብረት ስራ ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸዉን መግለጻቸዉን ከክፍለ ከተማዉ ት/ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s