ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የታብሌት ስጦታ እና ለተማሪዎች ለአንድ አመት የሚያገለግል የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ተደረገ፡፡
አለም አቀፉ የሴቶች ቀን “የጾታ እኩልነትን ዛሬ ማስፈን ለተሻለ እና ቀጣይነት ላለው ሀገራችን” በሚል መሪ ቃል በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ተከበረ። በመርሀ ግብሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ፣የትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራን ፣ተማሪዎችና የኢትዮ ቴሌኮም አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ቀኑ ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ46ኛ ጊዜ እንደሚከበር ታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በዝግጅቱ ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን ሴቶች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን ጥበብና አቅማቸውን በአግባቡ መጠቀም ከቻሉ የሚፈልጉበት ደረጃ መድረስ እንደሚችሉ ገልጸው ተማሪዎችም አሁን ያሉበትን የትምህርትም ሆነ የእድሜ ደረጃ ታሳቢ በማድረግ በትምህርታቸው ውጤታማ በመሆን ለሀገራቸው ጠቃሚ ዜጋ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በመማር ማስተማር ተግባሩ የሴቶች ተሳትፎም ሆነ ውጤታማነት እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ትኩረት አድርጎ ከሚያከናውናቸው ዋነኛ ተግባራት መካከል አንዱ የትምህርት ፍትሀዊነትን ማረጋገጥ መሆኑን በመግለጽ በዚህም በከተማ አስተዳደሩ በየትምህርት እርከኑ የሴትና ወንድ ተማሪዎች ተሳትፎ ተመጣጣኝ ደረጃ መድረሱን አስረድተዋል።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ሀና ጸጋዬ ኢትዮ ቴሌኮም አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በትምህርት ቤቱ በመገኘት ቀኑ በድምቀት እንዲከበር ላደረገው አስተዋጽኦ እና ለተማሪዎች ላበረከተው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
በፕሮግራሙ ኢትዮ ቴሌኮም 480 ለሚሆኑ ለትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ተማሪዎች ለአንድ አመት የሚያገለግል የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ከማድረጉ ባሻገር በ1ኛ መንፈቅ አመት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 10 ተማሪዎች የታብሌት ስጦታ አበርክቱዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!