ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስርዓተ ፆታ ማስረፅና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዕለቱን በማስመልከት ባዘጋጀው በዓል ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ቀኑን በማስመልከት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሴቶች ቀንን ስናከብር ከእለት ወደ እለት እየተሻሻለ የመጣውን የሴቶች ተሳትፎና ክብር መስጠት ማጠናከርና ለሴቶች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታችንን ማሳየት አለብን ሲሉ ገለፀዋል ::
ለሀገር ልማትና ሠላም መረጋገጥ የሴቶች ተሳትፎ ትልቅ እንደሆነ የገለፁት የፅህፈት ቤት ኃላፊው ሴቶች ስለሚችሉ በብቃት ተወዳድረው ባገኙት የስራ እድል ሁሉ ስኬታማ መሆን እንደቻሉ ማረጋገጥ የቻልንበት ጊዜ ነው ብለዋል ::
በወቅቱ ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሆኖ የሚከበርበት አላማና : የሴቶች እኩልነት መብትን የሚያሳዩ የኢትዮጵያ ሕግ አንቀፆችና ለግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቧል ::
ቀኑን በማስመልከትም ጥያቄና መልስ ውድድርና ግጥሞች ቀርበዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና እጩ ዶክተር ወ /ሮ አቶሜ አበበ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የሕይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል :: በመድረኩ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ለ 111ኛ በሀገራችን ለ46ኛ ጊዜ እየተከበረ እንዳለ ተመላክቷል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
