የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ግምገማ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ ተዘጋጅቶ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ግምገማ የደረሰበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን በመድረኩ ግምገማው በሚጠበቀው ደረጃ በመከናወኑ ውጤታማ ግምገማ መሆኑ ተገልፃል፡፡ ፡፡
የመጽሀፍ ግምገማው የደረስበትን ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ እና የቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በመገኘት ገምግመዋል።
እየተካሄደ ያለውን የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍም ሆነ የመምህር መምሪያ የመጽሀፍ ግምገማ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ እስካሁን ባለው ሂደት ገምጋሚ መምህራኑ በተዘጋጀላቸው የመገምገሚያ መስፈርት መጽሀፍቱን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአግባቡ በመገምገም የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸው የግምገማውን ውጤታማነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በቀጣይ ግምገማዉ ላይ የተነሱ ጉዳዮችን በማካተት ፤ የማጠቃለያ ስራዎችን በመከወን እና የጋራ የምክክር መድረክ በማከናወን የስራዉን ውጤታማነት ከዚህ የበለጠ ለማጎልበት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
የመጽሀፍ ግምገማው ከ17/06/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሙከራ ትግበራው ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች በተመረጡ መምህራንና በመጽሀፍ ዝግጅቱ ተሳታፊ በነበሩ መምህራን እንዲሁም በቢሮው የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያዎች በየትምህርት አይነቱ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች በእቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
