ቀን 22/6/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡፡

እንኳን ለ126ኛ ጊዜ ለሚከበረዉ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!  

አቶ ዘላለም ሙላቱ በመልዕክታቸዉ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም ፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ፋና ወጊ ፤ ሁሌም በትውልድ ልቦና ውስጥ ጎልቶ የሚታወስ እና በጀግንነት መዝገብ ውስጥ በደማቅ ቀለም የተፃፈ ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያውያንን ከዳር እስከ ዳር የሚያስተሳስርና ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችንን አጉልቶ የሚያሳይ የነፃነት አርማችን ነው ብለዋል።

ሀላፊዉ አክለዉም ይህ የአንድነታችን መገለጫ የሆነው የነፃነት ዓርማችን በጀግኖች አባቶቻችን ተጋድሎና መስዋዕትነት አኩሪ ታሪካችን ሆኖ እስከዛሬ ቆይቷል ። በቀጣይም  የኩራት ምንጫችን ሆኖ እንዲዘልቅ በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ታሪካዊ ሀገር ከተረከብን ከእኛ ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

ከተባበርን የማይታለፉ የሚመስሉ ችግሮችን ማለፍ አንደምንችል የአድዋ ድል ዋናኛ መሳያችን ነዉ ያሉት ሀላፊዉ በዚህ ዘመን በመደመር የጀመርነዉን የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል በማለት የአድዋ ድልን ደግመን ደጋግመን ለመድገም እንድንችል በትምህርት ዘርፉ ስራ ላይ የተሰማራን አኳላት በሙሉ ሳንታክት በመስራት ለሀገራችን ብልጽግና መረጋገጥ የበኩላችንን ሚና እንድንወጣ አደራ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡  

ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ይሁን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s