ቀን 16/6/2014 ዓ.ም

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ተራዝሞ የቆየው የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በመጀመሪያ ዙር የተሰጠው የ12ኛ ክፍል የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ኤጀንሲው ገልጿል።

ተማሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ መከናወኑንም ነው የገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል ብሏል ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ።

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙር (ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም) በተሰጠው የስነዜጋና ስነምግባር ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ስለታየበት የፈተና ውጤቱ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ጠቅሷል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለበትም ተገልጿል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ድረገፅ፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot – በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልዕክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።

4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293 ሺህ 865 ሴት 250 ሺህ 703 ድምር 544 ሺህ 568 ተማሪዎች ተሰጥቷል።

ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27 ሺህ 979 ሴት 26 ሺህ 456 ድምር 54 ሺህ 435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል።

በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617 ሺህ 991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321 ሺህ 844 ሴት 277 ሺህ 159 ድምር 599 ሺህ 003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s