የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኢንፎረሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ የአይ ሲቲ ባለሙያዎች በተግባር የተደገፈ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ስልጠናው በዋናነት በስኩል ኔት መሰረተ ልማት አጠቃቀምና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮችን መሰረት አድርጎ በቢሮው የአይ ሲቲ ባለሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ በለጠ ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
ዳሬክተሩ አክለውም ስልጠናው በየትምህርት ቤቱ በሁለተኛው መንፈቅ አመት ተማሪዎች የፕላዝማ ትምህርትን ጨምሮ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት መማር እንዲችሉ ሰልጣኞቹ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸው እስካሁን በአምስት ክፍለከተሞች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የአይሲቲ ባለሙያ ዎች ስልጠናውን መውሰዳቸውን ጠቁመው በቀጣይ ቀሪ ክፍለከተሞችም ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


