የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለቢሮው ሰራተኞች በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዙሪያ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር ለቢሮው ሰራተኞች ስልጠና መስጠት መጀመሩን ያሳወቀ ሲሆን ስልጠናው በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዙሪያ ሰራተኞች በቂ ግንዛቤ ይዘው እና መብትና ግዴታቸውን አውቀው ስራቸውን በአግባቡ መስራት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን የቢሮው የሰው ሀብትአስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ብዙነህ በቀለ ገልጸው አዋጁ በዋናነት ስለ ከባድና ቀላል የዲሲፒሊን ቅጣቶች፤ የአመት እረፍት አሰጣጥና ያለ ደሞዝ እረፍት አወጣጥን የተመለከቱ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን እንዳካተተ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ሰራተኛው አዋጆችን እና መመሪያዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ስራውን መስራት ከቻለ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ጠቁመው በዚህ ስልጠናም ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎች እስካሁን ያከናወኑዋቸው ተግባራት ከመመሪያና ደንብ አንጻር ምን እንደሚመስሉ እንዲሁም በቀጣይ ጊዜያትም ስራቸውን እነዚህኑ መመሪያዎች እና አዋጆችን ተከትለው መስራት እንዲችሉ እነደሚረዳቸውም አስታውቀዋል ፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!



