7ኛውን አለም አቀፍ የሚጥል ህመም ምክንያት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ፆታ ማካተትና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ከኬር ኢፕልፕሲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚጥል ህመም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ::
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ም /ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የሚጥል ህመምና ሌሎች መሰል ህመሞች በትምህርት ስርዓቱ ላይ የራሱ የሆነ መጥፎ አሻራ የሚያደርስ በመሆኑ ህመሙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ቢሮው አብሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል :: የስልጠናው ታሳታፊዎችም በቂ ግንዛቤ ወስደው ተማሪዎችና የትምህርት ማህበረሰቡን ማገዝ እንደሚገባቸው አሳስበዋል::
የኬር ኤፕሊፕሲ መስራችና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ እናት የእውነቱ በስልጠናው የሚሳተፉ የጤና ባለሞያዎች በትምህርት ቤት ውስጥ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ድጋፍ በማድረግ ሕፃናትን ለፍሬ ለማድረስ አቅም እንደሚሆኑ ገልፀዋል:: ወ/ሮ እናት አክለዉም ስልጠናው የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች በህክምና በመታገዝ የሕይወት አላማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረዋል ::
በእለቱ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነርቭ ሀኪም የሆኑት ዶክተር መስከረም ዳኛቸው የሚጥል በሽታ ምንነትና መንስኤ ፣ ምልክቶች ፣ የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥና መሰል ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል ::
በስልጠናው ከተመረጡ100 ትምህርት ቤቶች የመጡ የጤና ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

















