ቀን 9/6/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 200,000 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ።

የማስኩ ርክክብ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ፣የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሀይለገብርኤል ፣ የኮሌጁ ዲን አቶ ግሩም ግርማን ጨምሮ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የኮሌጁ ምክትል ዲኖች፣አሰልጣኝ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በርክክብ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ለተማሪዎቻችን ለአጠቃቀም ምቹ  በሆነ መልኩ ያዘጋጀውን ማስክ በማበርከቱ ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባው በመግለጽ በቀጣይ ጊዜያትም ኮሌጁ ለትምህርት ሴክተሩ መሰል ድጋፎች ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል  እምነታቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሀይለገብርኤል በበኩላቸው ኮሌጁ ወጣቶች ሙያዊ ክህሎት ኖሯቸው በተለያዩ የስራ መስኮች እንዲሰማሩ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የኮቪድ ወረርሽኝ በተማሪዎች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመከላከል ይህን የመሰለ ድጋፍ ማድረጉ ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንደሚያደርገው አስታውቀዋል።

ኮሌጁ ተማሪዎችን የማሰልጠን ተግባር ባሻገር በተለያዩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት እንደሚሳተፍ የኮሌጁ ዲን አቶ ግሩም ግርማ ገልጸው በዛሬው እለት በኮሌጁ አቅም የተዘጋጁ እና ለትምህርት ቢሮ የተረከቡ 200,000 ማስኮች 680,000 ብር እንደሚገመቱ አስረድተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s