የመምህር ያሬድ እና የተማሪ ናትናኤል የፈጠራ ስራዎች
የመምህር ያሬድ እና የተማሪ ናትናኤል በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚገኘዉ የአፍሪካ ህብረት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር እና ተማሪ ናቸዉ፡፡
በትምህርት ቤቱ የፊዚክስ መምህር የሆነዉ ያሬድ የቶርኖ ማሽን ለመስራት ችላል፡፡
በተግባር ስራዉ በትምህርት ቤቱ የሚታወቀዉ መምህር ያሬድ የሰራዉ የፈጠራ ስራ ለተለያዩ ስራዎች ቅርፅ ማውጫነት ፣የተለያዩ ፑሊዎችን እና ልዩ ልዩ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ነው።
በሌላ መልኩ የኒውተን ሰርድ ሎው ፊዚክስ ትምህርት ለፈጠራ ስራዉ እንዳገዘዉ የተናገረዉ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሆነዉ ናትናኤል እራስን ለመከላከል የሚያገለግል መሳሪያ በመስራት እና የሰራዉ መሳሪያ በተግባር አገልግሎት እንደሚሰጥ ለማሳየት ችላል፡፡
ለተሰሩት እንዲሁም ቀጣይ ለሚሰሩት የፈጠራ ስራዎች የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሰለሞን ይታየው ከጎናቸዉ መሆናቸውን እና በተሰረዉ ስራ መደሰታቸውን በመግለጽ አበረታተዋቸዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




