የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ትምህርት ጽ/ቤት ስር በሚገኙ የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች መካከል ልምድ ልውውጥ ተደረገ።
የልምድ ልውውጡ በአብዩት ፋና ትምህርት ቤት እና በግል ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን መካከል ተደርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ የክፍለ ከተማው የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ ፣ የወረዳ 10 የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሀይሉ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአብዩት ፋና ትምህርት ቤት የልምድ ልውውጡ ተካሄዳል።
በልምድ ልውውጡ ላይ አቶ አደፍርስ ኮራ እንደገለጹት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከተማሪ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው በቀጣይም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚረዱ ስራዎችን በጋራ መስራትና የልምድ ልውውጥን በማጠናከር ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ብሎም ለሀገር ተተኪ ትውልድ ለመፍጠር ተባብረን መስራት ይገባል ብለዋል።
በልምድ ልውውጡ የቤተ ሙከራ ፣የሙዚቃ ማዕከሎች፣የትምህርት ቤት ምድረ ግቢ ንፅህና አያያዝ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ የመረጃ አያያዝ ላይ ግብኝት ተደርጋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!





