ቀን 25/5/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ባልደረባ በሆኑት በአቶ ነጋ ገረመው ሀሳብን በጥበብ በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሀፍ ተመረቀ።

በመጽሀፉ ምረቃ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ በባላገሩ ቴሌቪዥን አንድሮሜዳ በሚል ርዕስ የሚተላለፈው ፕሮግራም አዘጋጅ የሆኑት መጋቢ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመጽሀፉ ደራሲ አቶ ነጋ ገረመው በምረቃ መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሀሳብን በጥበብ በሚል ተጽፎ የተመረቀው መጽሀፍ አራተኛ ድርሰታቸው መሆኑን ጠቁመው መጽሀፉ ከዝግጅት ጀምሮ ለህትመት እስኪበቃ ድረስ ከጎናቸው ለነበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በመጽሀፉ ይዘት ዙሪያ በቢሮው ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሰለሞን ወንድሙ እና ወይዘሮ ፍሬህይወት አሰፋ አማካይነት ገለጻ የተካሄደ ሲሆን መጽሀፉም በ140 ብር በሆነ ዋጋ ለአንባቢያን መቅረቡን ለማወቅ ተችሏል።

ደራሲው ቀደም ሲል በዓለም ውስጥ የተደበቁ እንቁዎች እና የኩሽ ሀያሉ ስሮው መንግስት፣ በዓለም ውስጥ የተደበቁ ዕንቁዎችና ኢትዮጵያ፣ትምህርት በህይወት ዑደት በሚሉ ርዕሶች ሶስት መጽሀፎች ማሳተማቸው ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s