የ12ኛ ክፍል ተማሪ ለሆነችዉ ቅድስት ጎሮሾ እና ለወላጅ እናታ እውቅና ተሰጣቸዉ፡፡
እውቅናዉን የሰጡት በልደታ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚገኘዉ የአፍሪካ ህብረት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና ሰራተኞች ናቸዉ፡፡
የትምህርት ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች እውቅናዉን የሰጡት በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተከታታይ የትምህርት ቀናት ጠዋት ጠዋት የሰንደቅ አላማ ስነ-ስርዓት በትምህርት ቤቱ በሚከበርበት ሰዓት ድምፁዋን ከፍ አድርጋ የኢትዬጽያ ህዝብ መዝሙር ለምታዘምረዉ ፣ ሀገር ወዳድነትን በተማሪዎች ላይ ለምታሰርጸዉ እና ለተማሪዎች እና ለትምህርት ማህበረሰቡ አርዓያ ለሆነችዉ ተማሪ ቅድስት ጎሮሾ እና ለወላጅ እናታ ለወ/ሮ አስናቀች ፍጅ ሲሆን በሰንደቅ አላማ ስነ-ስርዓት ላይ እውቅና በመስጠት የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶችን አብርክተዋል።
በመጨረሻም ተማሪ ቅድስት እና ወላጅ እናትዋ ወ/ሮ አስናቀች የኢትዮጽያ ሰንደቅ አላማ ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር በመምህራን እና በሰራተኞች ስም እንደተበረከተላቸዉ እና ለትምህርት ማህበረሰቡ መልዕክት እንዳስተላለፉ ከትምህርት ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


