ቀን 20/5/2014 ዓ.ም

የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የግብዓት ድጋፍ ለመርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት  አደረገ::

የየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኘዉ እና በጦርነቱ ምክንያት የወደመዉን መርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት ለማቋቋም እንዲቻል ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የግብዓት ድጋፍ አድርጋል፡፡

ጽፈት ቤቱ በስሩ ከሚገኙ ከ7ቱ 2ኛ ደ/ት/ቤቶች ያሰባሰበዉን ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ግብአት ድጋፍ ማድረጉን አሳውቃል::

ድጋፋን የሀብሩ ወረዳ ት/ፅ/ቤት ሀላፊ፣ የመርሳ 2ኛ ደ/ት/ቤት ር/መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት ከየካ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ተረክበዋል::

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዉ ት/ቤቱ  ሙሉ በሙሉ የወደመ መሆኑን ፣ የላብራቶሪ ፣ አይሲቲ ፣ የቤተ መፅሀፍት፣ የፕላዝማ  እና ሌሎችም ግብዓቶች ሙሉ ለሙሉ መዘረፉቸዉን እና መውደማቸዉን መመልከቱን ገልጻል::

የሀብሩ ወረዳ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ እና ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ምንም አይነት ድጋፍ እንዳልተደረገ በመግለጽ ለችግራችን ቀድሞ ለደረሰዉ ለየካ ክ/ከተማ አስተደዳር ት/ፅ/ቤት እና ለ2ኛ ደ/ት/ቤቶች ምስጋና ካቀረቡ በሀላ አሁን በተደረገላቸዉ ድጋፍ ትምህርት ቤቱን ትምህርት ለማስጀመር እንደሚችሉ ማሳወቃቸዉን ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s