የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የመጀመሪያ 6 ወራት የስራ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፡፡
የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በመጀመሪያ 6 ወራት ከክ/ከተማ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን ፤ ከመማር ማስተማሩ ስራ ጎን ለጎን ሃገራችን ኢትዮጵያ የገጠማትን ትልቅ ፈተና ለመወጣት እንደ ትምህርት ሴክተር ለመከላከያ ሠራዊት ደም በመለገስና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም ለተፈናቀሉ ወገኖች የቁሳቁስ፣ የገንዘብ እና የደረቅ ምግቦች ድጋፍ መደረጉን አስታውሰው “ዘመቻ በትምህርት ልማት ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል ከክ/ከተማ እስከ ት/ቤት ድረስ ሠፊ ንቅናቄ በማድረግ የትምህርት ማህበረሠቡ የ”NoMore” እንቅስቃሴ ላይ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም ከንፋስ ስልክ እና ከኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወደ ልደታ ክ/ከተማ የመጡ ተቋማትን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ኬክ በጋራ ቆርሰዋል፡፡
የትምህርት መረጃ አመራር ስርዓት ቡድን መሪ በሆኑት አቶ መንግስቱ አሳቦ በመጀመሪያ 6 ወራት ከቁልፍ እና ከአበይት ተግባራት አንፃር የተሠሩ ስራዎች ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በሪፖርቱ በአማራጭ መሠረታዊ እና ጎልማሶች ትምህርት ዙሪያ ፣ በት/ት ጥራት አሃድ ፣ በተ.ወ.ማ [ተማሪ፣ ወላጅ ማህበር] እና በመምህራን ማህበር የተሠሩ ስራዎች፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ከመፍታት አንፃር የተከናወኑ ተግባራት ፣ የት/ት ሽፋን ተደራሽነት፣ በህብረተሠብ ተሳትፎ የተሠበሠበ የሃብት መጠን፣ በ6ቱ መርሃ ግብሮች የተሠሩ ስራዎች፣ ከ8ኛ እና ከ12ኛ ክፍል ውጤት ማሻሻያ ልዩ ዕቅድ አንፃር የተተገበሩ ስራዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ከመድረክ መሪዎች ምላሽ ተሠጥቷል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


