የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት በዝግጅት ምእራፍ በ2013 በጀት ዓመት የታዩ ጥንካሬዎች ለማስቀጠል በ2014 አይቀጥሉም ተብለው የተቀመጡ ጉድለቶችን ለማረም አቅደን የገባን በመሆኑ በአፈፃፀም የተደረጉ ጥረቶች የተሻሉ ነበሩ ብለዋል :: አቶ ሳምሶን አክለዉም የተገኙ ውጤቶች ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ባሉ አካላት የጋራ ርብርብና ጥረት የተገኘ ነው ብለዋል ::
በዕለቱ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ከሶስት ዋና አላማዎችና አስራ ዘጠኝ ዋና ዋና ግቦች አንፃር በየዳይሬክቶሬቱ የተከናወኑ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌታሁን ለማ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል::
በሪፖርቱ በግማሽ ዓመት እንደ ቢሮ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ሊከናወኑ የሚገቡ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበዋል ::
የቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ያልተካተቱ ነጥቦች ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ተነስተዉ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


