የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ፆታዊ ጥቃትን መሰረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስርአተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ ዘውዴ እንዳሉት ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን በትምህርት ቤት ማሻሻል መርሃ ግብርና በራስ አቅም ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ት/ቤቶች ልምድ ለሌሎች በማሳየት ልምድ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ የተሰበሰበ ቼክ ሊስት ውጤት እንደሚያሳየው አሁንም በበቂ ሁኔታ የወንዶችና ሴቶች መፀዳጃ አለመለየትና ምቹ አለማድረግ እንዲሁም የሴቶች የንፅህና መጠበቂያና በወር አበባ ጊዜ እረፍት ለሚፈልጉ ተማሪዎች የተዘጋጀ ማረፊያ አለመኖርና የመሳሰሉ ችግሮች እንደሚታዩ የገለፁት የሥርአተ ፆታ ባለሙያዋ ወ/ሮ ትእግስት በሪሁን በስልጠናው የሚሳተፉ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ክበባት ሀላፊዎች በክትትልና ድጋፍ የታዩ ክፍተቶችን ለመሸፈንና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያሳዩ ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት እድል እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
ስልጠናዉ ፆታዊ ጥቃትን ከመከላከል ረገድ ዝቅተኛ አፈጻፀም የታየባቸው ት/ቤቶችን ለመደገፍ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ት/ቤቶች የአሰራር ዘዴዎች መውሰድ የበለጠ አቅም እንደሚፈጥር ተገልፃል፡፡
ስልጠናው ጥቃትን ከመከላከል አንፃር በ11 ዱ ክፍለ ከተሞች የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ የክ/ከተማና ወረዳ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ባለሞያዎች፤ ሱፐር ቫይዘሮችና ርዕሳነ መምህራን በሶስት ዙር እንደሚሰጥ ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!





