ቀን 10/5/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ ለመላዉ የክርስትና ዕምነት ተከታዩች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በክርስትና ዕምነት ተከታዩች የሚከበረዉን የብርሃነ ጥምቀት በዓልን አስመልከተዉ ባስተላለፉት የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ እንደገለጹት በመከናወን ላይ ያሉ የትምህርት ልማት ስራዎች ውጤታማነታቸዉ ሊረጋገጥ የሚችለዉ ጤናዉ በተጠበቀ የትምህርት ማህበረሰብ በመሆኑ ጤናዉ የተስተካከለ የትምህርት ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት ውስጥ የትምህርት ባለድርሻ አኳላት በዓለ ጥምቀቱን በሚያከብሩበት ጊዜ በዓሉ በጋራ መሰባሰብ የሚከበር በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በጤና ባለሙያዎች የሚመከሩ ጥንቃቄዎችን ያለምንም መዘናጋት በመተግበር ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

የትምህርት ስራ በአንድ አካል ጥረት ብቻ የሚሳካ አለመሆኑን የገለጽት ሀላፊዉ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በመቅረጽ እና ለሀገር እድገት አስተዋጽዎ የሚያበረክቱ የሀገር መሰረቶችን በማፍራት ተግባር ውስጥ የትምህርት ተቋማቶቻችንን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ተግተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ሀላፊዉ አክለዉም በዓሉም ሀገራችን ተገዳ በገባችበት የህልውና ዘመቻ ወቅት ላይ የሚከናወን በመሆኑ በጦርነቱ የተጎዱ አካላትን በመደገፍ ፣ በሆስፒታል የሚገኙ የመከላከያ ስራዊት አባላትን በመጠየቅ እና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ በመተሳሰብ መንፈስ ልናከብረዉ ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለአየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s