የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና ለገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት አዲስ ለገቡ ተማሪዎቸ የታብሌት ስጦታ ተበረከተ፡፡
የታብሌ ስጦታዉ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ አዲስ ለገቡ ተማሪዎቸ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተበርክቷል፡፡
ስጦታዉን ያበረከቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ሲሆኑ ተማሪዎች በዓሉን በሚያከብሩበት ጊዜ ሀገር ሰላም እንድትሆን እና በዓሉን በሰላም ለማክበር እንድንችል ብዙዎች ዋጋ የከፈሉ መሆኑን በማሰብ መሆን ይገባል ያሉ ሲሆን አክለዉም ሀገር ከተማሪዎች ብዙ የምትጠብቅ በመሆኑ ትምህርታቸዉን በአንድነት መንፈስ በመተባበር በአግባቡ በመማር ሚናቸዉን እንዲወጡ መምህራንም እያበረከቱት ያለዉ አስተዋጽዎን በማጠናከር እና ለሀገር ቅድሚያ በመስጠት ተማሪዎችን በማብቃት ሀገር የሚረከብ ዜጋ ለመፍጠር ተግተዉ እንዲሰሩ አደራ ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
