ቀን 28/4/2014 ዓ.ም

እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኪቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል በከተማዉ እየተሰጠ የሚገኘዉ ትምህርት በላቀ አፈጻጸም እንዲተገበር በየደረጃዉ ባለዉ የትምህርት ባለድርሻ አካል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉ ፣ የኪቪድ ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ለትምህርት ማህበረሰቡ እንዲደርስ መደረጉ፣ የተጀመረዉ የመማር ማስተማር ስራ ያለምንም ጸጥታ ችግር በመከናወን ላይ መሆኑ ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት በህግ ማስከበሩም ሆነ በህልውና ዘመቻዉ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ከደጀን እስከ ግንባር በመዝመት ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በማዋጣት የዘማች ቤተሰቦችን እና በጦርነቱ የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በመደገፍ ታሪካዊ አሻራ ማኖራቸዉ ፣ የውጭ ሀገራትን ተጽህኖ ለመቃወም የNO MORE ንቅናቄን መቀላቀላቸዉ ፣ ደረጃቸዉን የጠበቁ ትምህርት ተቋማት እዲኖሩ ያላሰለሰ ጥረት መደረጉ ፣ የ2013 ዓ.ም የሀገር አቀፍ 12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም ችግር እንዲሰጥ መደረጉ በ2014 የትምህርት ዘመን ከትምህርት መስክ ስራዎች ውስጥ ከተመዘገቡ ድሎች የሚጠቀሱ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በቀጣይ ይህንን ስራ በተሻለ እመርታ ማስቀጠል ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም በትምህርት ልማት ስራዉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በላቀ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ በ2014 የትምህርት ዘመን ሊተገበሩ የተጣሉ ግቦችን ለማሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸዉን ትውልድ የመቅረጽ ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሀላፊዉ አክለዉም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድሮ የሚከበረዉ የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ሀገራችን ተገዳ በገባችበት የህልውና ዘመቻ ወቅት ላይ የሚከናወን በመሆኑ በጦርነቱ የተጎዱ አካላትን በመደገፍ ፣ በሆስፒታል የሚገኙ የመከላከያ ስራዊት አባላትን በመጠየቅ ፣ አቅመ ደካሞችን በማገዝ እና መዓድ በማጋራት በመተሳሰብ መንፈስ ልናከብረዉ ይገባል ያሉ ሲሆን በዓልን መሰረት በማድረግ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተገቢዉን የኮቪድ መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ መዘንጋት የሌለበት መሆኑን በመጥቀስ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም ፣ የመተሳሰብ እና የብልፅግና እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s