ቀን 15/4/2014 ዓ.ም

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ባካሄደዉ ክትትልና ድጋፍ ላይ ውይይት አደረገ፡፡

በ19ኙ ግቦች ዙሪያ ለሁሉም የመንግስት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ፣ በ8ኛ እና በ12ኛ ክፍል ውጤት ማሻሻያ ልዩ ዕቅድ እና በተከናወኑ ተግባራት፣ በልዩ ፍላጎት ትምህርት፣ በውስጥና በውጪ በልምድ ልውውጦች፣ በመልካም አስተዳደር፣ ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ በሚደረጉ ጥንቃቄዎች፣ በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር፣ በምገባ ስርዓት እና በሌሎችም ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ክትትልና ድጋፍ መደረጉ በውይይቱ ተገልጻል፡፡

በክትትልና ድጋፉ የተገኙ ግኝቶች፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደረጉ ባለሙያዎች ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት ፣ በክ/ከተማ ደረጃ መፈታት የሚገባቸው የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች፣ የምገባ ስርዓቱ ውጤታማ ሆኖ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ፣ የቅዳሜ ማጠናከሪያ ትምህርት ለ8ኛ እና12ኛ ከፍል ተማሪዎች እየተሠጠ መሆኑን ፣ ከኮቪድ ጋር ተያይዞ ከጤና ቢሮ በወረደው አቅጣጫ መሠረት ሁሉም መምህራን፣ ር/መምህራን፣ የአስ/ሠራተኞች እና ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች ክትባት መከተባቸውን እንዲሁም ለወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ተከታታይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ ማድረግ በዋናነት ትኩረት ተደርጎ የሚሠራባቸው ስራዎች ይሆናሉ ብለዋል፡፡

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s