ቀን 13/4/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከርዕሰ መምህራን እና መጋቢ እናቶች ጋር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ በዋናነት በትምህርት ቤቶች መጋቢ እናቶች በምን መልኩ እንደሚደራጁ እና ኤጀንሲው ከመጋቢ እናቶች ጋር በሚዋዋለው ውል ይዘት ዙሪያ የተካሄደ ሲሆን ለውይይቱ መነሻ የሚሆን የመወያያ ሰነድ በምገባ ኤጀንሲ የተማሪዎች ምገባ ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ይመቸዋል ገብረ ፃዲቅ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አንቺነሽ ተስፋዬ እንዳስታወቁት መጋቢ እናቶችን እና ርዕሰ መምህራንን በጋራ ማወያየት ያስፈለገው ከምገባ ስርአቱ ጋር በሚታዩ ችግሮች ዙሪያ በመነጋገር የተሻለ አስራር ለመፍጠር ስለሚያስችል መሆኑን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ ለምገባ ስርአቱ ውጤታማነት በማሰብ በአንድ ተማሪ  ቀድሞ የነበረውን 16ብር ወደ 20 ብር ከፍ እንዲል በማድረጉ ለተማሪዎች የሚቀርበው የምግብ ሜኑ ማስተካከያ እንደሚደረግበትም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው የምገባ ስርአቱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ያለ ምንም ችግር በአግባቡ ተከታትለው ውጤታማ እንዲሆኑ ታስቦ መጀመሩን ገልጸው አገልግሎቱ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ወጥ ሆኖ መካሄድ እንዳለበት በመጥቀስ ትምህርት ቤቶችም ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው እና በጀቱ ለታለመለት አላማ መዋሉን መከታተል እንደሚገባቸውም  አስረድተዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s