የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብንና የብልፅግና ጉዞን ወደኅላ ሊጎትት የሚችል ምንም ኃይል እንደሌለ ወቅቱ ያስረዳናል ያሉ ሲሆን ይህን የጥፋት ቡድን በተሳሰረና በተባበረ ክንድ ድል በማድረግ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዲያሸንፍ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ብለዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ የመወያያ ሰነዱን በማቅረብ በአሸባሪዎች በተከፈተብን ሀገር የማፍረስ ወረራ አማካኝነት ተገደን ከገባንበት ጦርነት በመውጣት በሀገራችን ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ሰነዱ አቅም በመሆን ያገለግላል ብለዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘዉ ገብሩ በበኩላቸዉ ለሀገር ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እንዲቻል የአስተሳስብ ልዩነቶችን ለማጥበብ መሰል መድረኮች የሚኖራቸዉ ሚና የጎላ ነዉ ብለዋል፡፡
የውይይቱን አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ያደነቁት የቢሮው ሰራተኞችም አሸባሪው ቡድን ለረጅም ዓመታት የገነባውን የመከፋፈል መርህ ለማጥፋት አሁን ያለው የለውጥ አመራር ለአንድነት ለሰላምና ብልፅግና ሥራ ቅድሚያ በመስጠት ለብሄራዊ መግባባት ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል ::
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




