ቀን 11/4/2014 ዓ.ም

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና በየደረጃዉ ከሚገኙ የትምህርት መዋቅር የስራ-ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የውይይት አካሄደ።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ የፓርቲ ጉዳዮች ዘርፍ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ደንድር እና የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ ሲሆኑ የህወሓት አሸባሪ ቡድን ከሌሎች ፀረ-ሰላም ኃይሎች ጋር በመተባበር ሀገር ለማፈራረስ የጀመረውን ዕኩይ ሴራ ለማምከን የትምህርት ተቋማት በአርቆ አሳቢነተትና በበሳል አመራር ሰጭነት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ለሀገራቸው ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን አስተዋፅእ ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተጨማሪም እንደ ሀገር በውስጥና በውጭ ሀይሎች የገጠመዉን ፈተና በአሸናፊነት ለመወጣት እንዲሁም የተጎዱ አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መልሶ በማቋቋም ረገድ የትምህርቱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ ሊሆን እንደሚገባ ሀላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የትምህርት ተቋማት እና ምሁራን የ27 ዓመታት የህወሓት የጭቆና ዘመን ሰለባ መሆናቸዉን ገልፀዉ የህወሓት አሸባሪ ቡድን ሀገር ለማፈራረስ የጀመረውን ዕኩይ ሴራ በመረዳት እና ከመንግስት ጎን በመሰለፍ በሁሉም መስክ አንፀባራቂ ድሎችን እያስመዘገቡ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም መንግስት ለሚጠይቃቸው ማንኛውንም ድጋፍ ለማበረከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s