የእሳት አደጋ መንስኤዎችንና መወሰድ ያለባቸዉን ጥንቃቄዎች በተመለከተ ትምህርት ተሰጠ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 ትምህርት ጽፈት ቤት ስር በሚገኘዉ ልዕልት ዘ/ወርቅ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ከእሳት እና አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪ ተቋም በመጡ ባለሙያዎች በሰልፍ ስነ-ስርዓት ላይ የእሳት አደጋ መንስኤዎችንና መወሰድ ያለባቸዉን ጥንቃቄዎች በተመለከተ ትምህርት ተሰጠ፡፡
ስልጠናዉን አስመልከተዉ የትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ምክትል ርዕሰ መምህር ስልጠናዉን ለሰጡ ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካል በድንገት ሊከሰቱ የሚችሉትን የእሳት እና የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ከተከሰቱም በሃላ ጉዳት ሳያደርሱ ለመቆጣጠር እንዲቻል መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡
ስልጠናዉን የሰጡት ባለሙያዎችም ለትምህርት ቤቱ የእሳት ማጥፊያ ፎምና ሁለት ኳሶችን በስጦታ በተጨማሪ አበርክተዋል ።
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!


