ኢትዮጵያ ተገዳ ከገባችበት ጦርነት ወጥታ ወደ ልማትና ብልጽግና ጎዳና እንድትገባ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በከተማው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከተውጣጡ መምህራንና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳስታወቁት መንግስት ጦርነቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ዘላቂ ልማትና ብልጽግና ጎዳና ለመጓዝ በሚያደርገው ጥረት ምሁራን ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
ምክትል ከንቲባው አክለውም ምሁራንም ሆኑ ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን በማዳከም ተላላኪ መንግስት ለመፍጠር በአንዳንድ አገሮችና ሚዲያዎች የሚካሄደውን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመቀልበስ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውነታውን ማስረዳት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት በፍጥነት በድል አጠናቃ ወደ መደበኛው የልማት ጎዳና እንድትገባ የሁሉም ባለድርሻ አካል ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ይህ ውይይት ከምሁራንና ከተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር እንዲካሄድ መደረጉን ጠቅሰው ምሁራን ከሽብር ቡድኑ ወረራ ነጻ በወጡ አከባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ስነ ልቦና ከመገንባት ጀምሮ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ዳግም ወደ ስራ ለማስገባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚጠበቅባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የህልውና ዘመቻው በድል እንዲጠናቀቅ ከደጀንነት ጀምሮ በሞያቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው በጦርነቱ የደረሱ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን በማጥናት በታሪክ ተሰንደው ለትውልድ መማሪያ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አካባቢያችንን #እንጠብቅ
ወደ ግንባር #እንዝመት
መከላከያን #እንደግፍ
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!









