ቀን 7/4/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና መምህራን  ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ሱፐር ቫይዘሮች፣ ርዕሳነ መምህራን እና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳስታወቁት መንግስት ጦርነቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ ዘላቂ ልማትና ብልጽግና ጎዳና መጓዝ አለብን የሚል ጽኑ እምነት እንዳለው ገልጸው በጦርነቱ ነጻ የወጡ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ የትምህርት ሴክተሩ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህልውና ጦርነት በድል አጠናቃ ወደ መደበኛው የልማት ጎዳና እንድትገባ በሚደረገው እንቅስቃሴ የትምህርት ሴክተሩ ኃላፊነቱን ሊወጣ  እንደሚገባ ገልጸው በጦርነቱ የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የህልውና ዘመቻው በድል እንዲጠናቀቅ ከደጀንነት ጀምሮ ግንባር ለመዝመት እና በጦርነቱ የተጎዱ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s