ቀን 6/4/2014 ዓ.ም

በ79.2 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸዉ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤቶች ተመረቁ፡፡

የመጸዳጃ ቤቶቹ በ10 ትምህርት ቤቶች ለወንድና ሴት ተማሪዎች ምቹ በሆነ መልኩ የተገነቡ ሲሆን ወደ 79.2 ሚሊየን ብር የሚገመት ገንዘብ ወጪ ሆኖባቸዋል።

በመጸዳጃ ቤት ምርቃት መርሀ ግብሩ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መጋቢት 28 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳስታወቁት ለመማር ማስተማር ተግባሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማሰብ በ10 ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ የመጸዳጃ ቤቶችን በ79.2 ሚሊየን ብር ወጪ ለገነባው ኢጣሊያን ኤጀንሲ ፎር ዲቭሎፕመንት ኮኦፕሬሽን እና አጋሮቹ ምስጋና አቅርበው ግንባታዎቹ በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስታት መካከል ጠንካራ ወዳጅነት መኖሩን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም መሰል ፕሮጀክቶችን በመገንባት አጋርነታቸውን እንደሚያስቀጥሉ እምነታቸው እንደሆነም አስረድተዋል።

የኢጣልያን ኤጀንሲ ፎር ዲቭሎፕመንት ኮኦፕሬሽንን በመወከል ንግግር ያደረጉት ሚስ ኤልሳቤላ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃ ቤቶች መገንባታቸው ለተማሪዎች ጤና እና ንጽህና መጠበቅ አስተዋጽኣቸው ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ድርጅታቸው መጸዳጃ ቤቶቹን መገንባቱን ገልጸው ግንባታዎቹ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችም እንዲመቹ ተደርገው መገንባታቸውን አስገንዝበዋል።

በምረቃ መርሀ ግብሩ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ተወካይ ወይዘሮ ሜቲ ታምራት ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደፍርስ ኮራን ጨምሮ መምህራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ  

ወደ ግንባር  #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s