ቀን 6/4/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ከክፍለ ከተማ እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤትና ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር በኮቪድ 19 ክትባት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሀንጋቱ እንዳስታወቁት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በርካታ ሰዎችን ለሞትና ለተለያዩ አደጋዎች ማጋለጡን ተከትሎ ክትባቱ ለትምህርት ማህበረሰቡ እንዲሰጥ መወሰኑን ተከትሎ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ የትምህርት አመራሮች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ገልጸው አሁንም ቢሆን የወረርሽኙ ስርጭት ጉዳት ማድረሱን ስለቀጠለ ክትባቱን በተጠናከረ መልኩ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የክትባት ባለሙያው አቶ ሙሉቀን በትምህርት ሴክተሩ የክትባት አሰጣጥ ሂደቱ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በትምህርት ቤቶች ክትባቱን እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች እንደሚወስዱ በመግለጽ እስካሁን መከተብ ከሚገባቸው ተማሪዎች መምህራን የትምህርት ባለሙያዎችና ሌሎች የአስተዳደር ሰራተኞች አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎቹ አቶ አድማሱ ደቻሳ እና አቶ ሳምሶን መለሰ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ትምህርት ቤቶችን እስከ መዘጋት ደረጃ አድርሶ እንደነበረ በማስታወስ የመማር ማስተማር ስራው ዳግም ሲጀመር ማንኛውም አካል ክትባቱን እዲወስድ ተወስኖ እንደነበረ ጠቁመው ከክትባት ሂደቱ ጋር በተገናኘ በሚናፈሱ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች ምክንያት መከተብ ያለበትን ያህል ሰው ክትባቱን አለመውሰዱን እና ይህም በትምህርት ስራው ላይ የሚያስከትለው ተጽኖ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ  

ወደ ግንባር  #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s