ቀን 4/4/2014 ዓ.ም

ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር ውጤታማ ሆኖ በድል መጠናቀቁን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በጁንታዉ ቡድን እና በውጭ ሀይላት የተከፈተባትን ሀገር የማፍረስ ጦርነት እና ፕሮፖጋንዳን በልጆቻ ክንድ በመመከት ላይ ትገኛለች፡፡ በተለይም ደግም በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጁንታዉ በፈጸመዉ ከፍተኛ የሆነ የግድያና የመፈናቀል እኩይ ተግባር የተቆጣው የኢትዮጵያ ህዝብ በደጀንነት የሰራዊቱ አባል በመሆን፣ የዘማች ቤተሰብን በማገዝ ፤ ደም በመለገስ ፤ ስንቅ በማቀበል እና በመሳሰሉት ሁለንተናዊ ድጋፎች ትግሉን ተቀላቅሏል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን በውጭ ሀይላት የተከፈተዉን የፕሮፖጋንዳ ተጽህኖን ለመቃወም የ#NOMORE ንቅናቄን በመቀላቀል ሀገር የማዳኑ ተግባር በታላቅ ክብር እና ተነሳሽነት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ ስራ ውስጥ ደግሞ ከሀገር በላይ ምንም የለም በማለት የከተማችን የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች ፣ ማህበራት እና መንግስታዊ እና ምንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ታሪካዊ አሻራቸዉን በሀገራችን የወርቅ መዝገብ ላይ እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

በተለይም የከተማዉ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ምግቦች ፣ የንጽህና መጠበቂያዎች ፣ አልባሳት እና የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፎችን አድረገዋል፡፡ለዚህ ታላቅ ስራም ምስጋና ላቀርብላችሁ እወዳለሁ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተወሰነዉ ውሳኔ መሰረት ለአንድ ሳምንት የተቋረጠዉ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ላይ የከተማችን ተማሪዎች በዘመቻ ትምህርት ልማት ግንባር በመሳተፋቸዉ የአርሶ አደሮችን ሰብል የማሰባሰብ እና ቤተሰቦቻቸውን የማበረታት ፣ ደም የመለገሰ ፣ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና ዉሀ የማጠጣት፣ በት/ቤቶችና አካባቢ ላይ የፅዳት ዘመቻዎች የማድረግ ፣ በህልውና ዘመቻዉ ለተጎዱ የሰራዊቱ አባላት ድጋፍና ብርታት የመስጠት ፣ የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን የመደገፍ ፣ የስንቅ ዝግጅት ተግባራት ላይ የመሳተፍ፣ በየት/ቤቱ ስለ ሀገር ፍቅር እና ስለ ጀግንነት የሚዘክሩ የተለያዩ  መርሀ ግብሮችን ማካሄድ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በልዩ ሁኔታ ማክበር ችለዋል፡፡ በዚህም ዘመቻ ውጤታማ እና ታሪካዊ ስራን ለመስራት በመቻላችሁ ምስጋናዩ ላቅ ያለ ነዉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በዘመቻ ትምህርት ልማት ግንባር የትምህርት ማህበረሰቡ በሀገር ህልውና ዘመቻዉ ለተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የቁም እንስሳትን ድጋፍ ማድረጋቸዉ እጅጉኑ የሚያኮራ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የሀገር ወዳድነት መሳያ ነዉ፡፡ ተማሪዎችም በቦታዉ በመገኘት የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያዩበት እና ያጽናኑበት ፣ ለሀገር እና ለነገ ሀገር ተረካቢዎች ሲባል የተከፈለዉን መስዋዕትነት  እና የቁርጠኝነትን ጥግን የተረዱበት ታላቅ የተግባር የትምህርት ምዕራፍ ሆኖ አልፋል፡፡    

በመጨረሻም ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር ተጠናቆ ለአንድ ሳምንት ተቋርጦ የነበረዉ ትምህርት ዛሬ በከተማችን ሙሉ በሙሉ መጀመሩን እየገለጽኩኝ እና በቀጣይ ተከታታይ በሆኑ 5 ቅዳሜዎች ትምህርቱ የሚካካስ መሆኑን እያሳወኩኝ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ስታደርጉት ለነበረዉ ድጋፍ በሙሉ ምስጋናዩን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡

ኢትዩጵያ ታሽንፋለች!

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s