ቀን 1/4/2014 ዓ.ም

የለሚ ኩራ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ስልጠና የወሰዱ በጎ ፍቃደኛ የተማሪ ፖሊሶችን አባዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በትራፊክ ቁጥጥርና ደህንነት ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ ከ23ትምህርት ቤት የተውጣጡ የተማሪ ፓሊሶች ናቸው።

በምረቃ መርሀ ግብሩ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ከፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ወቅታዊውን የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎችን በዚህ መልኩ አሰልጥኖ ለስምሪት ዝግጁ ማድረጉ የሚያስመዘግነው ተግባር መሆኑን ገልጸው ተመራቂ ተማሪዎችም በየትምህርት ቤቶቻቸው የመማር ማስተማር ስራው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲካሄድ በወሰዱት ስልጠና መሰረት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መልኬ አለማየሁ በበኩላቸው የትምህርት ሴክተሩ ሀገራችን የገጠማትን የህልውና ፈተና ለመቀልበስ በሚደረገው እንቅስቃሴ የማይተካ ሚና እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው የዛሬ ተመራቂ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎችም በዚህ መልኩ ሰልጥነው ወደ ስራ መግባታቸው ትምህርት ቤቶች ከጸጥታ ስጋት ነጻ እንዲሆኑ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዋ ወይዘሮ ባዩማ ወርቁ ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር 1,200 ተማሪዎች ሰልጥነው ለዛሬው ምርቃት መብቃታቸውን ገልጸው በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎቹም የመማር ማስተማር ተግባሩ በጸጥታ ችግር ምክንያት እንዳይደናቀፍ ኃላፊነታቸውን በንቃት ሊወጡ ይገባል በማለት የአደራ መል አስተላልፈዋል።

Addis Ababa Education Bureau, [12/10/2021 1:59 PM]

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s