ቀን 28/3/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል  ሰበሰቡ።

የሰብል ስብሰባ መርሀ ግብሩ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በረክ ቀበሌ “ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር” መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ፣የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ተወካዮች፣አባ ገዳዎችን ጨምሮ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ  አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የሰብል ስብሰባ መርሀ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ የተቀደሰ አላማ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስከበር በየጦር ግንባሩ ተጋድሎ በማድረግ ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ቤተሰቦችን ስብል በመሰብሰብ ከጎናቸው መሆናችንን የምናረጋግጥበት ተግባር መሆኑን ገልጸው ይህ መርሀ ግብር ተባብረንና ተጋግዘን የሀገራችንን ልማትና ብልጽግና እንደምናረጋግጥ ሁነኛ ማሳያ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በሰብል ስብሰባ መርሀ ግብሩ ከ3,000 በላይ ሰው ተሳታፊ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ሴክተሩ በቀጣይ ቀናትም ደም የመለግስና የችግኝ እንክብካቤን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን የህልውና ትግሉ በድል እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ኃላፊነት እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ልዩ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ወይዘሮ ዝናሽ አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ማህበረሰብ አካላት በልዩ ዞኑ ተገኝተው የዘማች ሚኒሻ ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ላሳዩት አጋርነት በልዩ ዞኑና በዘማች ሚኒሻዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s