ቀን 27/3/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችና መምህራን የተሳተፉበት እና “ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር” በሚል መሪ ቃል ዘማች ቤተሰቦችን ለማገዝ ለሚጋዙ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት በአበበ ቢቂላ ስቴድየም የሽኝት መርሀ ግብር ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣የአዲ  አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ  የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ተ ሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሽኝት መርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የዛሬው ፕሮግራም የኢትዮጵያን ስም የሀሰት ዘገባ እየሰሩ የሚያጠለሹ አካላት እንደሚያስወሩት ሳይሆን ተማሪዎች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የሚሰበስቡበትና ለመከላከያ ሰራዊቱ ደም የሚለግሱበት እንዲሁም ሌሎች የበጎ ፍቃድ ተግባራት የሚያከናውኑበት መሆኑን ጠቁመው በዚህ ዘመቻ ተሳታፊ የሆኑ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚከናወኑ ተግባራት የበኩላቸውን አሻራ በማኖር ላይ መሆናቸውን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው አሁን ያጋጠመን ፈተና ኢትዮጵያ ከገጠሟት አደጋዎች አንዱና በአይነቱም የተለየ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ማህበረሰቡም ይህንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በዱር በገደሉ ለሚዋደቀው የመከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

ኃላፊው አክለውም ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሳተፉበት የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጸው በዋናነትም የዘማች ቤተስቦችን ሰብል የመሰብሰብ፣የደም ልገሳ ፕሮግራም፣ችግኞችን የመንከባከብ፣በስንቅ ዝግጅት መርሀግብሮች መሳተፍን ጨምሮ ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወኑ አስገንዝበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s