የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ማህበረሰብ አባላት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ሰንጋዎችን ድጋፍ አደረጉ፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ጠቅላላ ግምታቸው ከ 507 ሺ ብር በላይ የሆነ 12 ሰንጋዎችን አስረክቧል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ የትምህርት ማህበረሰቡ በጋራ ይህን መሰል ድጋፍ ማድረጉ ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ደጀንነት ያሳየ እንዲሁም ለሀገር አንድነት በጋራ መቆሙን የሚያሳይ በመሆኑ በአስተዳደሩና በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ስም ምስጋናየን አቀርባለሁ ብለዋል።
የትምህርት ማህበሰረብ አባላቱ ድጋፉን ያደረጉት በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ማህበሰረብ አባላት፣ተማሪዎች እና የወላጅ ኮሚቴ አባላት መሆናቸውን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
ሠራዊቱን ይደግፉ!
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

