ባገኘነው ድል ሳንዘናጋ ለአፍታም አይንና ጆሮአችንን ከአካባቢያችን ሰላምና ፀጥታ ላይ ማንሳት የለብንም ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::
በምስራቅ የጀመረው ድል በአጭር ጊዜ ጋሸናና ሸዋ ደርሷል ያሉት ከንቲባ አዳነች በታሪካዊው ድል ከፍተኛ የአመራር ሰጪነት እና የአገር ፍቅርን በተግባር ለገለፁት ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር ዐብይ አህመድ እንዲሁም ለከፍተኛ የጦር አመራሮች፤ ጀግናው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ ሀይሎች ያላቸዉን ወደር የማይገኝለት አክብሮትና አድናቆት ገልፀዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ መላው ህዝባችን ለተገኘው አንጸባራቂ ድል እንኳን ደስ አለን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
“መላው የከተማችን ነዋሪዎች ፣ የፀጥታ ሀይሎች እና አመራሮች ባገኘነው ድል ሳንዘናጋ ትኩረታችን የከተማችን ፀጥታ ላይ እናድርግ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድን በየሄደበት የፈሪ የጥፋት በትሩን በንጹሃን ዜጎች እና ንብረት ላይ የሚያደርስ ቡድን እስከወዲያኛው ወደ መረጠዉ ሲኦል እስኪሸኝ ለአፍታም አይንና ጆሮአችን ከአካባቢያችን ሰላምና ፀጥታ ላይ ማንሳት የለብንም” ብለዋል፡፡
“አሁንም ፀጉረ ልውጦችና ሰርጎ ገቦችን እንዲሁም በህገ ወጥ ያከማቹትን የጦር መሳሪያ እየተከታተልን ለህግ እናቅርብ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
ሠራዊቱን ይደግፉ!
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
