ለአሸባሪው ሕወሐት የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
በግንባር ተገኝተው በአንደኛው የጦር ግንባር የመጨረሻ ዕቅድ ላይ የመከሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአጠረ ጊዜና በአነስተኛ መሥዋዕትነት የኢትዮጵያ ድል የሚረጋገጥበትን መመሪያ ሰጥተዋል።
ሠራዊቱ በከፍተኛ ሞራል ላይ እንደሚገኝና ጠላትም እየተሸነፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጡ ሲሆን፣ በተደናበረ ዕቅድ የገባው ጠላት ተደናብሮ መውጣት እንደማይችል ተናግረዋል።
ለአሸባሪው ዓላማ የተሰለፉ ሁሉ እጃቸውን በመስጠት ራሳቸውን እንዲያተርፉ፣ የትግራይ ወላጆችም ልጆቻችን የት ደረሱ ብለው እንዲጠይቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላምና ልማት ነው። ወደዚህ ጦርነት የገባነው ተገድደን ነው። ማሸነፋችን ግን አይቀሬ ነው ሲሉ የኢትዮጵያን ድል አድራጊነት ገልጠዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
ሠራዊቱን ይደግፉ!
ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
