ቀን 19/3/2014 ዓ.ም

የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የማህበራዊ ተሳትፎ ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀዉ የስልጠና መርሃ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የሴቶችን ጥቃት መከላከል ማህበራዊ ተሳትፎን የሚጠይቅ በመሆኑ የስራ ክፍሉ ስልጠናው ከ 970 ሺ በላይ ተማሪዎችን ለሚያገኙ መምህራን መሰጠቱ ለውጤታማነቱ የራሱ ሚና እንዳለው ተናግረዋል:: ሰልጣኞችም በፆታዊ ጥቃት ዙሪያ ተጨባጭ መረጃ በመያዝ ሴቶችን ከጥቃት ለመከላከል ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ ዘወዴ ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 የሚከበረው የፆታዊ ጥቃት ቀን “ሰላም ይስፈን በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አሁን ይቁም ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ እና በሀገራችን እየተከበረ እንደሚገኝ ተገልጻል::

በስልጠናው ሴቶችን ለጥቃት የሚያጋልጡ ማህበራዊ ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ግላዊ ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል ::በተያያዘም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በማህበረሰብ ላይ የሚፈጥሩትን ተፅዕኖ አስመልክቶ የስልጠና ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ::

2 ቀን ቆይታ ባደረገዉ ስልጠና ላይ የ11ዱ ክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ባለሞያዎችና የትምህርት ቤት የስርዓተ ጾታ ክበባት ተጠሪዎች ተሳትፈዋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQዋለ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s