በመንግሰት የፋይናንስ አሰራር ስርዓት ዙሪያ ምክክር ተካሄደ

ቀን 21/06/2008 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ከአዲስ አበባ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር መሰረታዊ በሆኑ የመንግሰት ፋይናንስ አሰራር ስርዓቶች ዙሪያ ከቢሮዉ መካከለኛ አመራሮችና ከየስራ ሂደቱ የተወሰኑ በተለይም ከዝክረ ሃሳብ (proposal) ዝግጅትና ፋይናንስ ስራ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስራዎችን የሚሰሩ ባለሙያዎች በድምሩ 60 ከሚሆኑ ተሳታፊዎች ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ የግንዛቤ መስጨበጫ ምክክር አካሄደ፡፡
የምክክር መድረኩ ዋነኛ አላማ በትምህርት ልማት ዘርፍ በተሰማሩ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ዙሪያ ዘርፈ ብዙ የአቅም ግንባታ ስራዎች የሚሰሩና ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚደረገዉ የፋይናንስ ክፍያ ስራና የዝክረ ሃሳብ አዘገጃጀት ላይ በተደረገ ዳሰሳዊ ጥናት ከፋይናንስ አሰራር ጋር የተለያዩ ጉዳዮች ብዥታ የፈጠሩበት ሁኔታ በስፋት የተስተዋለ መሆኑን በመገንዘብ የፋይናንስ አሰራሩን ወጥ ለማድረግና ግልጽነትን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን በትምህርት ቢሮ የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የሥራ ሂደት ባለሙያ አቶ መክብብ በለጠ ገልጸዋል ፡፡
በተካሄደዉ የምክክር መድረክ ላይ የመንግስት የገንዘብ ክፍያ መርሆች፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ስርዓት አጠቃላይ ገጽታ፣ በፋይናንስ አሰራሮችና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከመድረክ አቅራቢዎች ሰፋ ያለ ገለጻ ተደርጓል፡፡ እንደ ተግዳሮት ከተነሱት ነጥቦች መካከል ለክፍያ የሚቀርቡ ዝክረ ሃሳቦች ተገቢዉን መስፈርት ያለሟሟላት፣ የስልጠና ተሳታፊዎች ሰዓት መቆጣጠሪያን በአግባቡ አለመከታተል፣ክፍያን በወቀቱ ቀርቦ ባለመቀበል ሂሳብ ለማወራረድ መቸገርና የመሳሰሉት አስተያየቶች በትምህርት ቢሮ የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ ስራ ሂደት ክፍል ቀርበዉ በተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ዉይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡ የተነሱት ችገሮች በሁሉም ስራ ሂደቶች ላይ የሚስተዋሉ ባይሆንም በአብዛኛዎቹ የስራ ሂደቶች የሚታዩ ችግሮች እንደመሆናቸዉ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ችገሮችን ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት መቅረፍ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡
የትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይለስላሴ ፍሰሃ በማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዉ እንደገለጹት ለተቋሙ የተመደበውን በጀት አጠቃቀም መመሪያን ጠንቅቆ ማወቅና በስራም ላይ ተግበራዊ ማድረግ የሁሉም የስራ ሂደቶች ሃላፊነት መሆኑን በማስገንዘብ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰዉ ፣ በቢሮዉ ያሉ ሰራ ሂደቶች ለሚያዘጋጁት ስልጠናም ሆነ ሌሎች መድረኮች የሚያስፈለጉ ወጪዎችን በተመለከተ የፋይናስ ስርዓትን መሰረት ያደረገ አሰራርን እንዲከተሉና ለሰራ የሚወጡ ወጪዎች ለሚመለከተዉ አካልና ለሚፈለገዉ ዓላማ ብቻ መዋሉን በጥብቅ መከታተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በማጠቃለያም ተሳታፊዎች ከምክክር መደረኩ ለቀጣይ ስራ መሻሻል ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት መቻላቸዉንና በተገኘዉ ልምድ መሰረት እንደሚሰሩ ጠቅሰዉ ለሁለቱ ቀናት ሲደረግ ስለነበረዉ የምክክር መድረክ አጠቃላይ ሁኔታና ለወደፊት ሊስተካከሉ በሚገቡ የፋይናንስ አሰራሮች ዙሪያ ሀሳብ በመለዋወጥ፤እንዲሁም በክፍያና ሂሳብ ደጋፊ ሰራ ሂደት የቀረቡ መጠይቆች ላይ አሰተያየት በመሥጠት የመርሃ ግበር ፍጻሜ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s